ከ5.6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሰባት መንገዶችን ደረጃ ለማሳደግና ለመገንባት የሚያስችሉ የኮንትራት ስምምነቶች ተፈረሙ፡፡

  • 0

ከ5.6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሰባት መንገዶችን ደረጃ ለማሳደግና ለመገንባት የሚያስችሉ የኮንትራት ስምምነቶች ተፈረሙ፡፡

Category : Projects

ከ5.6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሰባት መንገዶችን ደረጃ ለማሳደግና ለመገንባት የሚያስችሉ የኮንትራት ስምምነቶች ተፈረሙ፡፡

ግንባታቸው በአገር በቀል ተቋራጮች የሚካሄደው የፕሮጀክቶቹ ወጪም

ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው፡፡

የሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የመንገድ ዘርፍ ልማት መረሀ-ግብር አካል የሆኑት የነባሩን የአዲስ – ሞጆ – ሻሸመኔ – ሐዋሳ እና የአዋሽ – ሚሌ የመንገድ ፕሮጀክት ኮንትራት ሦስትና አራት እንዲሁም ሶሮቃ – ኢርጎዬ – አብርሃጂራ፣ አይካል – ዙፋን – አንገረብ እና በለስ-መካነብርሃን የመንገድ ፕሮጀክቶች ኮንትራቶችን ደረጃ ለማሳደግና ለመገንባት የሚያስችሉ የኮንትራት ስምምነቶች ዛሬ ግንቦት 18 ቀን 2008 ዓ.ም በባለሥልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተፈረሙ፡፡

626 ኪ/ሜትር ርዝመት የላቸው የአዲስ – ሞጆ – ሻሸመኔ – ሐዋሳ፣ የአዋሽ – ሚሌ የመንገድ ኮንትራት ሦስትና አራት፣ የሰሮቃ – ኢርጎዬ – አብርሃጂራ፣ አይከል – ዙፋን – አንገረብ እና በለስ – መካነብርሃን መንገዶች በጠጠርና በአስፋልት ደረጃ የነበሩ አንዲሁም የተወሰኑት አዲስ ሲሆኑ፣ ከመንገዶቹ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ እንዲሁም ካለው የትራፊክ ፍሰት አንፃር በአሁኑ ወቅት ደረጃቸው ወደ አስፋልትና ኮንክሪት አስፋልት ደረጃ እንዲያድግ ይደረጋሉ፡፡
7 projects

About Author

EACE

public relation head and web journalist

Leave a Reply

Publication Categories